ትዳር ዱሮ እና ዘንድሮ
ትዳር የማህበረሰባዊ እሴቶቻችን መሰረት ነው፡፡ አላማችን መልካም ግንኙነቶች አብበው፣ አፍርተው ፍሬአቸውን ማየት ነው፡፡
Kum Neger Staff
ሃበሻዊ ባህላችን ትዳርን የሚያከብረዉን ያህል ማንኛውንም ማህበራዊ ተቋም አያከብርም፡፡ ሰው ኣድጎ እንደ ሙሉ ሰው የሚቆጠረው ትዳር ሲይዝ ነው ማህበረሰባዊ ግዴታዎች የሚጣሉበትም ካገባ በኋላ ነው፡፡ ከዛ በፊት እንደ ሙሉ ሰው ሰለማይቆጠር ሰርግ፣ ለቅሶ ቤት፣ ድግስ እና መሰል ማህበራዊ ተሳትፎዎች ላይ እንዲሳተፍ አይጠበቅበትም፡፡ ጠለቅ ብሎ ላላሰበው ሰው ይሄ ማህበረሰባዊ አተያይ ያላገባውን ክፍል የሚያገል ይመስላል፡፡ በእርግጥም አንዳንድ ጊዜ የእውነትም ሊያግል ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰፋ አድርገን ካየነው የትዳር መሰረታዊ እሴቱ ምንድን ነው ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡
ሁላችንም እንደምናውቀው በህይወታችን ዉስጥ ብዙ ዋጋ የምንሰጣቸው፣ የምንሳሳላቸው፣አንዳንዴም ህይወታችንን ጭምር ልንሰጥላቸው የምንችል እሴቶች (values) አሉ፡፡ ሃይማኖት፣ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ትምህርት፣ ስኬት ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ የእነዚህ ሁሉ መሰረታቸው ሲፈተሽ ግን ትዳር ነው ፡፡ በየትኛውም እምነት ፈጣሪ መሰረተው ተብሎ የሚታመነው ማህበረሰባዊ ግንኙነት ቤተሰብ ነው ፡፡ የቤተሰብ ዋናው መሰረት ደግሞ ትዳር ነዉ፡፡ ፈጣሪ እኛ በራሳችን የምሰረትናቸውን ብሔሮች፣ ድርጅቶች፣ ተቋማት ወዘተ ተመስረቱ ፣ ሁኑ ብሎ አልፈጠረም ፡፡ ትዳርን ግን ሁኑ ፣ ተጋቡ ብሎ ራሱ የመሰረተው ህይወት ነው ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ሌሎቹ ተቋማት በሙሉ የሚገነቡት ትዳር በሚባለው መሰረት ላይ ስለሆነ ነው ፡፡ አብዛኛው የዓለማችን ችግሮች የሚመነጩት ደግሞ ባግባቡ ካልተመራ ትዳር ነው ፡፡ አብዛኛው ችግሮቻችን መነሻ ምክንያታቸው ሌላ ቢመስልም ወደ ውስጥ ሲጠና ግን የተረጋጋ የልጅነት ጊዜን ካለማሳለፍ እና የተረጋጋ የትዳር ህይወት ካለመኖር የሚመነጩ ናቸው ፡፡ ይህን ሰለተረዱም ይመስላል በዓለም ላይ ያሉ አብዛኞቹ ማህበረሰቦች ለትዳር ትልቅ ዋጋ የሚሰጡት፡፡
በባህላችን ትዳር የሚመሰረትባቸውን መንገዶች ሰናይ እንደየጊዜው ተለዋዋጭ ናቸው፡፡ ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ለትዳር ያላቸው ክብር እና ለቤተሰብ ፣ ለወግ፣ ለስርአት ያላቸው ትልቅ ቦታ ነው ፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ እናቶቻችን እና አባቶቻችን ሳይተዋወቁ ፣ ሳይፋቀሩ ይጋቡ ነበር፡፡ ለትዳር ካላቸው ክብር የተነሳ ብዙ ችግሮችን ችለው እየተጎዱም ጭምር ትዳርን አስቀጥለዋል ከእነሱ ቀጥሎ የመጡት ትውልዶች ደግሞ እንደ ዘመኑ ራሳቸው ተዋውቀው ትዳር ለመመስረት ቢወስኑም ፤ በክብር ወላጆቻቸውን አስፈቅደው ተመርቀው ትዳርን ይመሰርታሉ፡፡ ሁለቱን ዘመኖች አንድ የሚያደርጋቸው ሁለቱም ተጣማሪዎች በአካል ተዋውቀው በሩቅም ቢሆን እንኳን ተያይተው ነው ወደ ፍቅር የሚገቡት ፡፡
የእኛ ዘመን ላይ ስንደርስ ደግሞ ዓለም ተለውጣ በኢንተርኔት ዘመን አንድ መንደር ሆና ሰዎች ወደ ብዙ ሃገራት ተበትነው የሚኖሩባት ሆናለች፡፡ በዚህ ሁሉ መካከል ታዲያ የማይለወጠው ማህበረሰባዊ እሴታችንን እንደያዝን ግን ደግሞ ዘመኑ ባመጣቸው መንገዶች ለመገናኘት ፤ የኛን እምነት እና እሴት የሚጋራን የህይወት አጋር ለማግኘት እንሞክራለን፡፡ ብዙ ሰዎችም ተሳክቶላቸው ለቁም ነገር በቅተው ፣ ወልደው ስመዋል፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ ብዙዎች ያገራቸው ልጆች ጋር የሚገናኙበት የሚተዋወቁበት መንገድ ሩቅ ሆኖባቸው ይቸገራሉ፡፡ ብዙ የመገናኛ መድረኮች (platforms) ቢኖሩም አንደኛ የእኛን ባህል፣ ማንነት፣ ቋንቋ ያላገናዘቡ በመሆናቸው ፤ በተጨማሪ ደግሞ ጨዋነት የጎደላቸው መድረኮች በመሆናቸው የእኛን ማህበረሰብ በአግባቡ ሊያገለግሉ አልቻሉም፡፡ የዚህ ዋነኛ መፍትሄ ደግሞ ፻ በ፻ (100%) ደህንነቱ የተረጋገጠ፣ ግላዊ የሆነ እና የእኛን ማህበረሰብ እሴቶች ያገናዘበ መድረክ (platform) ነው፡፡
የቁም ነገር መስራቾችም ይህንን የራሳቸውን የጓደኞቻቸውን እና የአካባቢያቸውን ችግር ለመቅረፍ በማሰብ የቁም ነገርን መተግበሪያ (application) ለአገልግሎት አውለዋል ፡፡ ምኞታችን መልካም ግንኙነቶች አብበው፣ አፍርተው ፍሬአቸውን ማየት ነው፡፡ መልካም የመጣመሪያ ጊዜ !!!
ቁም ነገርን በGoogle Play Store እና Apple App Store ማግኘት ይቻላል፡፡